Your Cart

ጥሞና- Daily Devotional in Amharic- E-BOOK- Download NOW

On Sale
$9.99
$9.99
Added to cart
ስንቶቻችን በየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብና የመጸለይ ልምምድ አለን? የእግዚአብሔርን ቃል (መጽሐፍ ቅዱስን) ዕለት ዕለት ማንበብ እጅግ ብዙ ጠቀሜታ አለው። ለእግር መብራት የሆነው ቃል መንገድን ያበራል። የእግዚአብሔርን ቃል የሚያነብ ሰው የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት ጆሮዎቹ የተከፈቱ ናቸው። ግሳፄንና ምክርን እውቀትንም ያገኛል። ከሁሉ በላይ የፈተናን ቀን ማሸነፍ  የሚቻለው በእግዚአብሔር ቃል ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዲያቢሎስ በተፈተነ ጊዜ “እንዲህ ተብሎ ተጽፏል” በማለት በእግዚአብሔር ቃል ሀይል ሰይጣንን እንደኮረኮመው መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ዳዊትም በመዝሙሩ ‘አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ ሰወርሁ’ (መዝ (119፡19) በማለት በልብ የተሰወረ ቃል በሀጢያትና በፈተና ቀን አፅንቶ እንደሚያቆም ይናገራል። ሰው የፈጠረውን የእግዚአብሔርን ምሳሌ እንዲመስል ወደ ፍፁም ሙላትም እንዲያድግ በየቀኑ የእውቀት ምንጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ሊመገብ ይገባዋል።

ለዚህ እድገት ይረዳ ዘንድ ይህን “ጥሞና” የተሰኘና ለዕለታዊ ጸሎትና ቃል ምንባብ የሚረዳ ባለ 365 ገጽ (አንድ ገጽ ለአንድ ቀን) መጽሐፍ እነሆ ብያለሁ። መልካም ንባብ!

ምንተስኖት ገበየሁ ወልደአማኑኤል (ዶ/ር)
You will get a PDF (3MB) file